ESOG News

ESOG 2021: ESOG's 29th Annual Conference to be Held

The Ethiopian Society of Obstetricians and Gynecologists (ESOG) will be conducting its 29th annual conference beginning the 14th of February, 2021. The  Pre-Conference CMEs, which will be a series of virtual sessions, will kick start the conference on February 14 stretching over February 15, 2021. The main event of the conference the plenary session and the panel on the theme of the Conference- Mitigating the Impacts of COVID-19 on RMNCAH Services will be conducted on February 16, 2021. The main event allows both in-person attendances at Hilton Hotel while the sessions are to be broadcasted virtually to attendees around the nation and beyond. The following day will be occupied a series of Scientific Sessions and the State of the Art Lecture. The conference concludes with a special virtual social gathering.  

ህጻናት ጤናማ ክብደት እንዲኖራቸው እንርዳቸው፡፡

  • በኢሶግ እየተዘጋጀ በአዲስ አድማስ ጋዜጣ ላይ በሚታተመው ለአንቺና ላነተ አምድ ላይ የታተመና በኢሶግ ሚዲያና ኮሙኬሽን ኦፊሰር ጸሃይ ተፈረደኝ የተዘጋጀ፡፡

  • አስታውሱ…. በየቀኑ የሚኖሩ ትናንሽ ለውጦች ውጤታማ ያደርጋሉ፡፡

ክብደት ያላቸውን ህጻናት መመልከት በአለም በየጊዜው እየጨመረ ሲሆን በተለይም በአለፉት ሁለት አስርት አመታት ቁጥራቸው ቀላል የማይባሉ ልጆች በተለያዩ ሀገራት ክብደታቸው ከፍ እያለ መሆኑን CDC ያወጣው ዘገባ ያሳያል፡፡ የህጻናት ክብደት በአሉበት እድሜም ይሁን በወደፊት ህይወታ ቸው ለጤናቸው ጉዳትን ሊያስከትል ይችላል፡፡

ወላጆች፤አሳዳጊዎች እና አስተማሪዎች ህጻናቱ ጤናማ ክብደት እንዲኖራቸው ለማስቻል የጤ ናማ አመጋገብን ልማድ እንዲያዳብሩ ሊረዱዋቸው ኃላፊነት አለባቸው፡፡ ለምሳሌም ህጻናቱ በምግባቸው ውስጥ በካሎሪ የበለጸጉ ምግቦችን በተመጠነ መልክ እንዲያገኙ ማድረግ አንዱ ህጻናቱ ጤናማ ክብደት ሊያገኙ ከሚችሉባቸው መንገዶች መካከል ነው፡፡

ህጻናት ለአካል ብቃታቸው ተገቢውን እንቅስቃሴ እንዲያደርጉ እና ቴሌቪዥን ወይንም ስልኮች ላይ ከመቆየት እንዲቆጠቡ ማድረግ፤በቂ በሆነ ሁኔታ እንቅልፍ እንዲያገኙ ሁኔታዎችን ማስተ ካከል ህጻናቱ ጤናማ ሆነው ሊያድጉ ከሚችሉባቸው መንገዶች ተጠቃሾቹ ናቸው፡፡

ክብደታቸው የጨመረ ህጻናትን በሚመለከት ኪሎአቸው እንዲስተካከል ማድረግ ህጻናቱ በጤና ማነት እንዲያድጉ የማድረግ ግብ ያለው ነው፡፡ ሆኖም ግን ህጻናቱ ክብደታቸው ስለጨመረ ከሕ ክምና ባለሙያዎች ምክር ውጪ የክብደት መቀነስ ፕሮግራም ውስጥ ማስገባት ትክክል አይሆ ንም፡፡ ህጻናቱ በየትኛው መንገድ ክብደታቸውን መቀነስ እንዳለባቸው ለማወቅ ስለአመጋ ገባቸው ወይንም ስለአካል ብቃት እንቅስቃሴው ባጠቃላይም ስለእለት ውሎአቸው ባህርይ ከህክምና ባለ ሙያዎቻቸው ጋር መምከር እጅግ ጠቃሚ መሆኑን ወላጆች እንዲሁም አሳዳጊዎች ሊረዱት ይገባል፡፡

በዚህ እትም፤

  • ስለ ጤናማ አመጋገብ ልማድ፤
  • ካሎሪ የበዛባቸውን ምግቦች ስለመመጠን፤
  • ህጻናቱ ጤናማ የሆነ የአካል እንቅስቃሴ እንዲያደርጉ ወይንም እንዲጫወቱ፤እንዲንቀሳቀሱ ማድረግ፤
  • በቴሌቪዥን ፊልም የሚያዩበት ወይንም በስልኮች ጨዋታ የሚጫወቱበትን ጊዜ መቀነስ፤
  • በበቂ ሁኔታ መተኛታቸውን ማረጋገጥ የሚሉትን ጠቃሚ ነጥቦች ታነቡ ዘንድ ወደአማርኛ መልሰነዋል፡፡

ጤናማ አመጋገብ፤

ህጻናት ጤናማ የሆነ አመጋገብን እንዲለምዱ ለማድረግ

  • አትክልቶችንና ፍራፍሬዎችን እንዲሁም ጥራጥሬ የሆኑ ምግቦችን በብዛት እንዲመገቡ ማድረግ፤
  • ቀይ ስጋ፤ዶሮ፤አሳ፤እና ባቄላ የመሳሰሉትን ፕሮቲን ያለባቸውን ምግቦች እንዲመገቡ ማድረግ፤
  • ውሀ በደንብ እንዲጠጡ ማድረግ፤
  • ስኩዋር እና ስብ ያለባቸውን ምግቦች እንዳይደፍሩ ወይንም በብዛት እንዳይመገቡ ማድረግ፤

ከላይ የተጠቀሱትን መንገዶች መከተል በአመጋገብ ምክንያት ሊከሰት የሚችለውን አግባብ ያልሆነ ውፍረት ለማስወገድ ይረዳል፡፡በየቀኑ የሚኖሩ ትናንሽ ለውጦች ውጤታማ ያደርጋሉ፡፡

በካሎሪ የበለጸጉ ምግቦችን መመጠን፤

በስብ እና በስኩዋር የበለጸጉ እንዲሁም ጨው የበዛባቸውን ምግቦች ህጻናቱ እንዲወስዱ ማድ ረግ ጤናማ ስላልሆነ ከዚህ ልማድ እንዲርቁ ማድረግ ጤናማ ህጻናትን በማሳደግ ረገድ እጅግ ጠቃሚ ነው፡፡ ህጻናቱ እነዚህን ምግቦች አልፎ አልፎ ብቻ እንዲመገቡ ማድረግ ብልህነት ነው፡፡

ለምሳሌም ለህጻናቱ ምግብ ሲዘጋጅ 100 ወይንም ከዛ ያነሰ ካሎሪ እንዲኖረው ዝቅተኛ ስብ፤ ዝቅተኛ ስኩዋር እንዲሆን በሚከተለው መንገድ ቢሰናዳ ጥሩ ይሆናል የሚለውን ማሳያ የ CDC ገጽ ያስነብባል፡፡

  • አንድ የሻይ ስኒ ካሮት፣ብሮኮሊ እና 2 የሾርባ ማንኪያ የአሳማ ስጋ፤
  • መካከለኛ አፕል ወይንም ሙዝ፤
  • አንድ የሻይ ስኒ የወይን ፍሬ፤
  • አንድ አራተኛ የሻይ ስኒ ቱና፤
  • ጥቂት በቤት የተዘጋጀ እንደ ቆስጣ እና ጎመን የመሳሰሉ አረንጉዋዴ ቅጠሎች፤

በዚህ መንገድ የቀረቡ ምግቦች ህጻናቱ እንዳይወፍሩ ይረዳል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ህጻናቱ እንዲጫወቱ ወይንም እንዲሯሯጡ ማድረግ ለአእምሮአቸው ደስታን ከመፍጠሩ በተጨማሪ በጤንነታቸው በኩል ብዙ ጥቅሞችን እንዲያገኙ ይረዳል፡፡ ስለዚህም በተለይም በተወሰኑ ጊዜያት አቅም በፈቀደ ወደ አካል ብቃት እንቅስቃሴ ማዘውተሪያ ቦታዎች ህጻናቱን መውሰድ የሚከተሉትን ጥቅሞች እንዲያገኙ ይረዳል፡፡

  • አጥንትን ለማጠንከር፤
  • የደም ግፊትን ለመቀነስ፤
  • ጭንቀትና መረበሽን ለማስወገድ፤
  • የራስን መተማመን ለማጎልበት ወይንም ስሜትን የተሟላ ለማድረግ፤
  • ክብደትን ለመቆጣጠር ይረዳል፡፡

አልፎ አልፎ እንደሚታየው ከሆነ ወላጆች ልጆቻቸው ከቤት ወጥተው ከሰፈር ልጆች ጋር ከሚጫወቱ ይልቅ በቤት ውስጥ ቆይተው ፊልም ቢመለከቱ ወይንም በስልክ ወይንም በኮምፒ ዩተር ጌም ቢጫወቱ የሚመርጡ መሆናቸው እየታየ ነው፡፡ ለዚህ የሚሰጡት ምክንያትም ልጄ የተለየ አመል ወይንም ልማድ ይዞ ይመጣል የሚል ነው፡፡  ነገር ግን ልጆች በአካባቢያቸው ሊጫወቱባቸው የሚችሉባቸውን ቦታዎች ከካካባቢው ህብረተሰብ ጋር ተባብሮ በማዘጋጀት ወይ ንም በመ ደበኛ በተያዘ ፕሮግራም ወደ ህጻናት ማጫወቻ ቦታ ወስዶ እንዲጫወቱ ማድ ረግ ካልተቻለ ለህጻናቱ ጤንነት ጉዳት እንዳለው በመረዳት መላ መፈለግ ይጠቅማል፡፡

በእድሜያቸው ከ3-5 አመት የሆኑ ህጻናት በቀን ውሎአቸው ለእንቅልፍ ካላረፉ በስተቀር ቀኑን ሁሉ ማለት በሚያስችል ሁኔታ በከፍተኛ ሁኔታ ሲጫወቱ ሲሯሯጡ የሚውሉ ናቸው፡፡ እድሜያቸው ከ6-17 አመት የሚሆኑት በቀን ውስጥ እስከ 60 ደቂቃ ለሚሆን ጊዜ አካላቸውን ማንቀሳቀስ እና መጫወት ይገባቸዋል፡፡

  • እንደ ኤሮቢክስ ያሉ እስፖርቶችን መስራት የልብ ምትን ለማስተካከል ይረዳል፡፡
  • የአጥንት ጥንካሬን ለመጨመር እንደ እሩጫ ወይንም ዝላይ የመሳሰሉትን እስፖርቶች መስራት ይጠቅማል፡፡
  • የጡንቻ ጥንካሬዎችን ለማምጣት ደግሞ እንደ ከፍታ መውጣት ወይንም መሬት ላይ ፑሽ አፕ የመሳሰሉ እስፖርቶችን መስራት ይጠቅማል፡፡

ህጻናት አዋቂዎችን እንደምሳሌ ይወስዳሉ፡፡ ስለዚህም ልጆቻችሁን እስፖርት መስራት እንዲለምዱ ለማድረግ እራሳችሁ እየሰራችሁ እንዲበረታቱ ማድረግ ይጠበቅባች ሁዋል፡፡ ጤናማ አመጋገቦችን እንዲለምዱ ጤናማ የሆነ ምግብን እየተመገቡ ማሳየት ያስፈልጋል፡፡

ህጻናቱ ቴሌቪዥን ወይንም ቪዲዮ በቀን ከ2 ሰአት በላይ መመልከት የለባቸውም፡፡ እድሜያ ቸው ሁለት እና ከዚያ በታች የሆኑት ግን ቴሌቪዥን እንዲያዩ አይመከርም፡፡ ህጻናት ክብደታቸው ከመጠን ያለፈ እንዳይሆንና ጤናማ እንዲሆኑ አመጋገባቸውንና የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎቻቸውን በመከታተል ጥሩ እንቅልፍ እንዲኖራቸው ማድረግ ይጠቅማል፡፡